top of page
AboutEISAA.gif

Association

Making a Difference

Ethiopian Information System Audit Association (EISAA) is a non-profit organization that promote the Information Systems Audit practice in Ethiopia.

The primary purpose of the association is to build capacity development with in individual, organization and Ethiopian information environment level within the context of Information System Audit.


MISSION

  1. የኢንፎሜሽን ሲስተም ኦዲት እውቀትንና ሙያን በኢትዮጵያ ውስጥ ማስተዋወቅና ማበልጸግ

  2. የኢንፎሜሽን ሲስተም ኦዲት ሙያ ከሚመለከታቸው የኢትዮጵያ የመንግስት ተቋማትጋር የኢንፎሜሽን ሲስተም ኦዲትንና ተጓዳኝ ሃሳቦችን በሚመለከት የፖሊሲ እቅድ እና ትግበራ ሥራ ላይ የሙያ ድጋፍ መስጠት

  3. በኢንፎሜሽን ሲስተም ኦዲት ሙያ የተማረ የሰው ሃይል ማደራጀትና ማበልጸግ

  4. በኢንፎሜሽን ሲስተም ኦዲት ባለሙያዎች መካከል የግንኙነት የሙያ መድረክን መፍጠርና በባለሙያዎች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲደረግ ማመቻቸት

  5. በኢንፎሜሽን ሲስተም ሙያ ብቁ ኦዲተር በመሆን የተረጋገጡ (Certified) ባለሙያዎችን ማሳደግ

GOAL

  • በአባላቱ መካከል ግንኙነት መመስረት እና የኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲተርን ተጓዳኝ የሙያና የልምድ ልውውጥን ማመቻቸት

  • የኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ፣ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ደህንነት (Information security) ፣ የአደጋ ስጋት አስተዳደር (Risk Managment) እና መልካም የኢንፎርሜሽን አስተዳደርን (good IT governance) ማጎልበት እና ማስተዋወቅ

  • በማህበሩ ውስጥ የሙያ ብቃቶችን ፣ የፍላጎት ደረጃ እና ችሎታዎች ማሳደግ እና ማዳበር

  • የአባላቱን የሙያዊ ትብብር እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን ማስተዋወቅን ማመቻቸት

  • የኢትዮጵያን “ቻርተር” ምስረታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለወደፊቱ ብቁ ኦዲተር ለመሆን የተረጋገጡ ባለሙያዎችን ማሳደግ እና ለወደፊቱ “የኢትዮጵያ ቻርተር” በ Information Systems Audit and Control Association (ISACA) ዋና ድርጅት ሥር አባል እንዲሆን ጥረት ማድረግ

  • በኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ስርዓት ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን በመከታተል መፍትሄ መሻት፣

  • አገራችን በኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ስርዓት ፍላጎት ራሷን እንድትችል ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ፣

  • የኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ስርዓት በግልም ሆነ በወል ከውጪ ባለሃብቶች ጋር ጥምረት በመፍጠር የጎለበተ እውቀት አቅርቦት እንዲፈጠር ማበረታታት እውቀት ማበልጸግን የሚጠቅም ጥናት ማካሄድ፣

  • በኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ስርዓት መረጃን መሰብሰብና ለተጠቃሚዎች ማድረስና ከመንግስት ዓካላት ጋር በጋራ መስራት፣

  • በአገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከሚገኙ አቻ ማህበራት ጋር ግንኙነት መፍጠር፣

  • በመንግስት ደረጃ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ስርዓት ጥራት ቁጥጥርና ሰርቲፊኬሽን ላይ በሚደረገው ጥረት እገዛ ማድረግ፣

  • አባላት ለተሰማሩበት የሥራ መስክ ትምህርትና አዳዲስ ሃሳቦችን ሊያገኙ የሚችሉበትን መድረክ መፍጠር፣

  • የማህበሩን አላማ ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዱ ማንኛውንም ሥራ ማከናወን ናቸው፡፡

Association: About Us
bottom of page