top of page
Bylaw1_edited_edited.png

Highlights of Rules of the Association

የኢትዮዽያ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ማህበር = (ኢኢሲኦማ)
የእንግሊዝኛ ስም Ethiopian Information System Audit

Association (EISAA)

የኢትዮዽያ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ማህበር

መተዳደሪያ ደንብ

መግቢያ
የኢትዮጵያን የኢንፎርማሽን ሲስተም የጥራት ብቃትን በተሻለ ልምድ ላይ የተመሰረተ የሥራውጤት እንዲሆንና ይህንንም የጥራት
ደረጃና የኢንፎርሜሽን ደህንነትን ለመጠበቅና ቀጣይነት እንዲኖረው በማሰብና ይህንንም ከግብ ለማድረስ በሚደረገው ጥረት
አስተዋጽኦ ለማድረግ ሲባል የኢትዮዽያ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት የሙያማህበር (ኢኢሲኦማ) የእንግሊዝኛ ስም
Ethiopian Information System Audit Association (EISAA) ማደራጀት ታምኖበታል፡፡

መቋቋም
የኢትዮዽያ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት የሙያማህበር 26.12.2013 ዓ.ም ተቋቁሟል፡፡

ስያሜ
በዚህ መተዳደሪያ ደንብ የተቋቋመው ማህበር “የኢትዮዽያ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት የሙያማህበር (ኢኢሲኦማ)
የእንግሊዝኛ ስም Ethiopian Information System Audit Association (EISAA) በሚል ስም የሚጠራ ሲሆን
ከዚህ በኋላ የሙያማህበር ወይም አሶሴሽን ተብሎ ይጠቀሳል፡፡

ማህበሩ የተቋቋመው ለሚከተሉት አላማዎች ነው፡፡
1. በአባላቱ መካከል ግንኙነት መመስረት እና የኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ተጓዳኝ የሙያና የልምድ ልውውጥን ማመቻቸት
2. የኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ፣ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ደህንነት (Information security) ፣ የአደጋ ስጋት አስተዳደር (Risk Managment) እና መልካም የኢንፎርሜሽን አስተዳደርን (good IT governance) ማጎልበት እና ማስተዋወቅ
3. በማህበሩ ውስጥ የሙያ ብቃቶችን ፣ የፍላጎት ደረጃ እና ችሎታዎች መጠገን እና ማዳበር
4. የአባላቱን የሙያዊ ትብብር እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን ማስተዋወቅን ማመቻቸት
5. የኢትዮጵያን “ቻርተር” ምስረታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለወደፊቱ ብቁ ኦዲተር ለመሆን የተረጋገጡ ባለሙያዎችን ማሳደግ እና ለወደፊቱ “የኢትዮጵያ ቻርተር” በ Information Systems Audit and Control Association (ISACA) ዋና ድርጅት ሥር አባል እንዲሆን ጥረት ማድረግ
6. በኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ስርዓት ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን በመከታተል መፍትሄ መሻት፣
7. አገራችን በኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ስርዓት ፍላጎት ራሷን እንድትችል ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ፣
8. የኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ስርዓት በግልም ሆነ በወል ከውጪ ባለሃብቶች ጋር ጥምረት በመፍጠር የጎለበተ እውቀት አቅርቦት እንዲፈጠር ማበረታታት እውቀት ማበልጸግን የሚጠቅም ጥናት ማካሄድ፣
9. በኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ስርዓት መረጃን መሰብሰብና ለተጠቃሚዎች ማድረስና ከመንግስት ዓካላት ጋር በጋራ መስራት፣
10. በአገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከሚገኙ አቻ ማህበራት ጋር ግንኙነት መፍጠር፣
11. የኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ስርዓት ጥራት ቁጥጥርና ሰርቲፊኬሽን ላይ በሚደረገው ጥረት እገዛ ማድረግ፣
12. አባላት ለተሰማሩበት የሥራ መስክ ትምህርትና አዳዲስ ሃሳቦችን ሊያገኙ የሚችሉበትን መድረክ መፍጠር፣
13. የማህበሩን አላማ ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዱ ማንኛውንም ሥራ ማከናወን ናቸው፡፡

አጠቃላይ የማህበሩን ደንብ በዚህ ሊንክ ያገኛሉ።

Rules of the Association: Academics
bottom of page